ወበዛቲ ዕለት ሰኔ 5
እንኳን ለኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ ብሶይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን።
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
ቅዱስ አባ ብሶይ ሰማዕት
ቅዱሱ አባታችን ከዘመነ ሰማዕታት ጣፋጭ ፍሬዎች አንዱና ግንባር ቀደሙ ነው:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ማጠናቀቂያ አካባቢ #ታግሕስጦስና_ክሪስ የሚባሉ ክርስቲያኖች ነበሩ:: በቀናው የጽድቅ ጐዳና ቢኖሩም ከጋብቻ በሁዋላ ለ17 ዓመታት መውለድ አልቻሉም::
የ17 ዓመት ልመናቸውን የተመለከተ እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አበሰራቸው:: "ሕጻኑ ለሰማዕትነት ተመርጧልና ብሶይ በሉት" አላቸው:: ብሶይ በተወለደ በ7 ዓመቱ ወላጆቹ ይማር ብለው ወደ ገዳም ወሰዱት:: በገዳም ውስጥ መጻሕፍትን አጥንቶ ዲቁናን ተሾመ:: ወደ ዓለም ተመለስ ቢሉትም እንቢ አለ::
ከባልንጀራው ቅዱስ ዼጥሮስ ጋር ለ21 ዓመታት በድንግልና: በተጋድሎ: ጾምና ጸሎትን እያዘወተሩ ኖሩ:: ቅዱስ ብሶይ 28 ዓመት በሞላው ጊዜ መልዐኩ የተናገረው የትንቢት ዘመን ደረሰ:: በርካታ ምዕመናን ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ታረዱ:: ወደ እሳትም ተጣሉ:: ሞትን የፈሩ ደግሞ በየዱር ገደሉ ተሰደዱ::
ቅዱስ ብሶይም በሚያውቁት ሰዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ:: ድንገት ከሰማይ ፍጡነ ረድኤት ወሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ደረሰለት:: "አይዞሕ! እኔ እስከ መጨረሻው ካንተ ጋር ነኝ" አለው::
የጦር መኮንኑ ክርስቶስን እንዲክድ አባበለው:: ቅዱሱ ግን ጣዖታቱ የአጋንንት ማደሪያ መሆናቸውን በገሃድ ነገረው:: መኮንኑ ቢበሳጭ ወታደሮቹ እንዲጨምቁት አዘዘ:: ደሙ እየወረደ ገረፉት:: በፊትና በሁዋላ ብረት አድርገው ሥጋውን ጨፍልቀው እሥር ቤት ውስጥ ጣሉት:: ሊቀ መላዕክት መጥቶ ዳስሶ አዳነው::
መኮንኑ እርሱን ማሰቃየት ደከመው:: #የቅዱሳን_ሕይወት ግርም ይላል:: ተገራፊው እያለ ገራፊው: ስቃዩን የሚቀበለው እያለ አሰቃዩ ይደክመዋል:: ይሕንን ነው አባ ጽጌ ድንግል:-
"እመዐዛ ጽጌኪ ድንግል ውስተ ዐውደ ስምዕ ዘሰክረ:
ውግረተ አዕባንኒ ይመስሎ ሐሰረ:
እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ" ያለው::
ቅዱስ ብሶይን ካንዱ መኮንን ወደ ሌላው እያመላለሱ አሰቃዩት:: አካሉን ቆራረጡ-ዐይኑን በጋለ ብረት አወጡ-በምጣድ ቆሉት-በጋን ውስጥ ቀቀሉት:: እርሱ ግን በፈጣሪው ፍቅር የጸና ነውና ሁሉን ታገሰ:: በነዚሕ ሁሉ የስቃይ ዓመታት ቁራሽ ዳቦ እንኩዋ አላቀመሱትም:: በረሃብ ቀጡት እንጂ:: ለርሱ ግን ምግቡ የክርስቶስ ስም ነበር::
በመጨረሻ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ አንገቱን በሰይፍ አስመታው:: ሥጋውንና የተቆረጠ አንገቱን ገንቦ (ጋን) ውስጥ ከቶ ጣለው:: የቅዱሱን አካል የያዘችው ጋን ግን በእግዚአብሔር ቸርነት: ማንም ሳይሸከማት ከመሬት ከፍ አለች:: ለ20 ቀናት ተጉዛ ከሶርያ ግብጽ (ቦሃ) ደረሰች:: ክርስቲያኖች ተቀብለው ሲከፍቷት የቅዱስ ብሶይ ራሱና አንገቱ ተጣብቆ ተገኝቷል:: በክብርም አሳርፈውታል::

አምላከ ቅዱሳን ከሰማዕቱ ቅዱስ ብሶይ በረከት ያሳትፈን:: በምልጃውም ይቅር ይበለን::
ሰኔ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፡-
1.ቅዱስ አባ ብሶይ (ኃያል ሰማዕት)
2.ቅድስት ማርታ ለባሲተ ክርስቶስ (በቅድስናዋ የተወደሰች: በስደት ያረፈች እናት ናት)
3.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ
4.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት

No comments:
Post a Comment